ነገ የሚጠናቀቅውን የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች አማራ ከወዲሁ በበላይነት አጠናቀቀ።

መጋቢት 17፣ 2008

ነገ በሀዋሳ ፍፃሜውን የሚያገኘውን  5ኛውን የመላ ኢትዮጵያ  ጨዋታዎች አማራ ከወዲሁ በበላይነት አጠናቀቀ።

በ 5ኛው የመላው ኢትዮጵያ  ጨዋታዎች መጠናቀቂያ  ዋዜማ ላይ ኦሮሚያ  አራት ወርቅ፣ አዲስ አበባ ሁለት ወርቅ፣ አማራና  ደቡብ  አንድ አንድ ወርቅ አግኝተዋል።

ከወንዶች የእግር ኳስ በስተቀር ሁሉም ጨዋታዎች ፍፃሚያቸውን አግኝተዋል።

ነገ በወንዶቹ  የእግር ኳስ ፍፃሜ  አምስተኛው የመላ  ኢትዮጵያ  ጨዋታዎች ፍፃሜውን የሚያገኝ  ይሆናል።

በዚህም መሰረት የዘንድሮውን ውድድር አማራ  በበላይነት ለማጥናቀቅ የሚያስችለውን  ውጤት 58 ወርቅ አስመዝግቧል። ኦሮሚያ  በ53 ወርቅ ብርቱ ፉክክር አድርጎ  በሁለተኛነት ሲጨርስ፣   የደቡብ  ብሄር ብሄረሰቦች ደግሞ በ43 ወርቅ ሶስተኝነትን አዟል።

ባለፉት ሁለት ሳምንታት በሀዋሳ ደምቆ  የነበረው ውድድርም  አዲስ አበባ  ከድሬዳዋ  በሚያደርጉት የወንዶች የእግር ኳስ ፍፃሜ  ማጠናቀቂያውን ያገኛል።

ሪፖርተር፥  አዘመራው ሙሴ  

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች