አርሰናል በፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቀቀ

ግንቦት 07፣2008

አርሰናል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ  ሁለተኛ ሆኖ  አጠናቀቀ።

የ2015/16 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማጠናቀቂያ 9 ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገዋል።

የማንቸስተር ዩናይትድ እና በርንማውዝ ጨዋታ ግን በደህንነት ስጋት የተነሳ ለሌላ ጊዜ ተዛውሯል።

በስታዲየሙ ፈንጂ ይሆናሉ ተብለው የተጠረጠሩ ቁሶች በመታየታቸው ነው ጨዋታው የተሰረዘው።

ዛሬከ1 1 ሰዓት ጀምሮ  ነው ዘጠኙም የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች  የተደረጉት።

ቀድሞ ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋገጠው ሌሰተር ሲቲ ከቼልሲ ጋር ያደረገው ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ  ውጤት አጠናቋል።

አስቶን ቪላን 4 ለ 0 የረታው አርሴናል ፣ቶተንሃም በኒውካስትል 5 ለ 1 በመሸነፉ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ሌስተርን ተከትሎ በ 71 ነጥብ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል።

ማንቸስተር ሲቲ ከስዋንሲ 1 ለ 1፣ ዋትፎርድ ከሰንደርላንድ 2 ለ 2፣ ዌስትብሮም ከሊቨርፑል 1 ለ 1 አቻ ተለያይተዋል። ሳውዝአምፕተን ክሪስታል ፓላስን 4 ለ 1 እንዲሁም ስቶክ ዌስትሃምን 2 ለ 1 ማሸነፍ ችለዋል።

ሌስተር ሲቲ ሁለት ጨዋታዎች እየቀሩት በ81 ነጥብ በመሰብሰብ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ዋንጫ  በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀድሞ  መውሰዱ  ይታወሳል ።

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች