ዜኔዲ ዚዳን ሪያል ማድሪድን የሻምፒዮንስ ሊግ ባለድል አደረገው

ግንቦት 21፣2008

በቅርቡ  የአሰልጣኝነት መንበሩን የተረከበው ዜኔዲ ዚዳን ሪያል ማድሪድን የሻምፒዮንስ ሊግ ባለድል አደረገው።

የማድሪድ ክለቦች የሆኑት ሪያል ማድሪድና አትሌቲኮ  ማድሪድ ትናንት ምሽት በሚላን ስታዲዬም  ድራማዊ የሆነ  ምሽት አሳልፈዋል።

ሪያል ማድሪድ በሰርጂዮ ራሞስ አማካኝነት በመጀመሪያው  ግማሽ የጨዋታ  ጊዜ  ቀድሞ መምራት ቢችልም፣ አትሌቲኮ  ማድሪዶችም በሁለተኛ  ግማሽ ተቀይሮ በገባው ያኒክ ካራስኮ  አማካኝነት አቻ የሚያደርጋቸውን ግብ ሲያገኙ ሙሉ  የጨዋታው  ጊዜ  ያለመሸናነፍ ነበር የተጠናቀቀው።  

ሁለቱ ክለቦች በሙሉ  የጨዋታ  ጊዜ    በአንድ እኩል ውጤት በመጨረሳቸው ፣ወደ  ጭማሬ  ሰዓት ለመሸጋግር ተገደው ነበር። ይሁንጁ  በዚህኛውም ጊዜ  መሸናነፍ  ባለመቻላቸው ድራማዊ ትእይት  በታየበት ፍፁም ቅጣምት ሪያል ማድሪድ  5 ለ3 በሆነ  ድምር ውጤት ለ11ኛ ጊዜ የአውሮፓ  ሻፒዮንስ ሊግ ባለድል ሆኗል።

ሁለቱም ክለቦች በፍፁም ቅጣት ምቱ  የመጀመሪያዎቹን ሶስት ግቦች በተከታታይ ማስቆጠር መቻላቸው ነበር የጨዋታውን ፍፃሜ ይበልጥ ልብ ሰቃይ ያደረገው።ይሁንጂ  አትሌቲኮዎች አራተኛ እድላቸውን በማምከናቸው  ማድሪዶች ደግሞ  ሁሉንም እድል በመጠቀማቸው በክሪስቲያን ሮናልዶ  የማሳረጊያ  ቄንጠኛ  ጎል  የዘንድሮውን  የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ባለድል መሆናቸው አውጀዋል።  

ዜኒዲ ዚዳንም በተጨዋጭነትና  በአሰልጣኝነት የሻንፒዮን ሊግን  ዋንጫ የወሰደ  ሁለተኛው አሰልጣኝ ሆኖ  ተመዝግቧል።

አትሌቲኮ  ማድሪድ በበኩሉ  ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ   ሶስት ያህል ጊዜ  ደረሶ የተሸነፈ ክለብ ሆናል።

ምንጭ ፥ ቢቢሲ

 

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች