ዮሚፍ ቀጄልቻ በፓሪሱ የ3ሺ ሜ የዳይመንድ ሊግ አሸናፊ ሆነ

ነሐሴ 22፣ 2008

ሊጠናቀቅ ሁለት ዙር በቀረው የዳይመንድ ሊግ ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ ትናንት ፓሪስ ላይ የ3ሺ ሜትር አሸንፏል።

ዮሚፍ ከአራት የአገሩ  ልጆች ጋር ወደ  መሮጫ  ሜዳ  ገብቶ 7:28.19  በሆነ  ሰዓት በአንደኝነት ጨርሷል።

ዮሚፍ በርቀቱ ያስመዘገበው ሰዓት ከ20  አመት በታች በክብረ  ወሰንነት ተይዞለታል።በመደበኛው ዘርፍ ደግሞ መሪ  የሚባል ሰዓት ነው ዮሚፍ ያስመዘገበው። 

ከዮሚፍ ጋር አብሮ  የሮጠውና  በሪዮው ኦሎምፒክ በ5 ሺ ሜትር ነሃስ ያመጣው ሀጎስ ገ/ ህይወት ሶስተኛ  ሆኖ ጨርሷል።ለሙክታር እድሪስ ግን የትናንቱ  ፍክክር አልቅናውም።ውድድሩን በ7ኛነት ጨርሷል።

በሴቶች 1500 ሜትርየተሳተፉት ኢትዮጵያዊያኑ ደረጃ ውስጥ ሳይገቡ ተመልሰዋል። ዳዊት ስዩም፣  በሱ ሳዶ፣ ጉዳፍ  ፀጋይና አክሱማዊት እምባየ ከአምስተኛ  እስከ 14ኛ  ባለው  ደረጃ ውጥ  አጠናቀዋል።

በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል  የተሳተፉት ሶፍያ  አሰፋና እቴነሽ ዲሮ ደግሞ  በቅደም ተከተል 5ኛና 10ኛ ሆነው አጠናቀዋል። እነ ሶፍያ በሮጡበት ርቀት ኬንያዊቷ  ሩት ጃቤት ክብረ ወሰን በመስበር ጭምርነው ያሸነፈችው።

የዳይመንድ ሊግ ውድድር በቀጣይ በዙሪክና  ብራስልስ ተካሄዶ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ከኢትዮጵያ በወንዶች ሙክታር እድሪስ በ5 ሺህ ሜትር  30 ነጥብ እየመራ የርቀቱ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቶታል። ዮሚፍ በ22  ነጥብ ፣ሀጎስ ደግሞ በ15 ነጥብ ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።

በተመሳሳይ አልማዝ አያናም በሴቶች ምድብ ርቀቱን 30 ነጥብ በመምራት ላይ ትገኛለች።

ምንጭ፥ ዳይመድ ሊግ 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች