ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በአለም አቀፍ የማራቶን መድረኮች የበላይነትን ወስደው አሸነፉ

ጥቅምት 29፣2009

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሶስት አለም አቀፍ የማራቶን መድረኮች የበላይነትን ተቆጣጥረው አሸነፉ።

ትናንት በአውሮፓ  የደብሊንና ፍራንክ ፈርት ማራቶን ፣ በኢስያ ደግሞ የሻንጋይ ማራቶን ውድድሮች ተካሂደው ኢትዮጵያዊያን ደምቀውበታል ውለዋል።

በተለይ በአይረላንድ የደብሊኑ ማራቶን በወንዶች ከ1-3ኛ  ያለውን ደረጃ በመውሰድ የበላይነታቸውን አረጋግጠዋል።  

አትሌት ደረጀ ደበሌ በ2:12:08 ርቀቱን በቀዳሚነት ሲጨርስ፣ ደረጀ ኡርጌቻና አሰፋ በቀለ  ደግሞ ሁለተኛ እና  ሶስተኛ በመሆን ተከታትለው በመግባት በርቀቱ የበላይነትን ወስደው አጠናቀዋል።

በሴቶች ምድብ ደግሞ አትሌት እህተ  ገብረየስ  በ2:32:31 ሰዓት በማስመዝገብ ሁለተኛ  ሆና ርቀቱን በድል ጨርሳለች።

በሌላ  በኩል ጀርመን ላይ በተካሄደው የፍራን ክፈርቱ ማራቶን ማሚቱ ዳስካ 2:25:27 በሆነ ሰዓት ርቀቱን በቀዳሚነት አጠናቃለች።

ለጀርመን የሮጠችው ፋቴ  ቶላ ደግሞ አትሌት ማሚቱን ተከትላ በሁለተኛነት አጠናቃለች።

በፍራንክፈርቱ ማራቶን ዕድል ለኢትዮጵያዊያን ወንድ አትሌቶች ሳትሆን  ቀርታ ከ1-3ኛ ያለውን ደረጃ  ከንያዊያኑ ወስደዋል።

በቻይና በተካሄደው የሻንጋዩ  ማራቶን ደግሞ አትሌት ሮዛ ደረጃ 2:31:16 በሆነ  ሰኣት የግሏን ምርጥ ሰዓት በማሻሻል ጭምር ለማሸነፍ ችላለች።አትሌት  ውዴ አያሌው ደግሞ በሶስተኛነት በማጠናቀቅ የርቀቱ ባለክብር ሆናለች።

ምንጭ ፥ የአለም አቀፉ የትሌቲክስ ፌደሬሽንና አይሬሽ ታይምስ

  

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች