በሁሉም የአገሪቱ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ነገ ሕዝባዊ የጎዳና ላይ ሩጫ ይካሄዳል

የካቲት 25፡2009

በሁሉም የአገሪቱ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች  ነገ ሕዝባዊ የጎዳና ላይ ሩጫ ይካሄዳል፡፡

"ጊዜ የለንም እንሮጣለን ፤ ለህዳሴ ግድባችን እንቆጥባለን" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው ሕዝባዊ የጎዳና ላይ ሩጫ እሁድ የካቲት 26/2009 ዓ.ም ጠዋት በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ  የከተማ አስተዳደሮች ይካሄዳል፡፡

የወጣቶና ስፖርት ሚኒስተር ፣ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚንስቴር ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ፅፈት ቤት በጋራ ባዘጋጁት አገር አቀፍ ሕዝባዊ ሩጫ ላይ ከ650 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ይሳተፈሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከጠዋቱ 12 ሰአት ጀምሮ በመላው አገሪቱ የሚደረገው ውድድር ሴቶች ለህዳሴ ግድቡ ግንባታ ያላቸውን ሚና እንዲሁም በየአመቱ የሚከበረውን የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ባደረገው ሕዝባዊ የጎዳና ላይ ሩጫም  ከ80 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በከተማዋ ከጠዋቱ 12 ሰአት ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ በሁሉም አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚያመሩ ጎዳናዎች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑና በመስቀል አደባባይና በዙሪያው ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ሪፖርተር፡- ናትናኤል ፀጋዬ

          

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች