ኢትዮጵያዊያን ሩዋጮች በሁለቱም ፆታ የራባት አለም አቀፍ ማራቶን አሸናፊ ሆነዋል

የካቲት 27፣2009

ኢትዮጵያዊያን ሩዋጮች በሁለቱም ፆታ የራባት አለም አቀፍ ማራቶን አሸናፊ ሆነዋል፡፡

ትላንት በሞሮኮ ራባት በተካሄደው  የ42 ኪሎ ሜትር የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያኑ በሴትም በወንድም በበላይነት አጠናቀዋል፡፡

በውድድሩ ኬንያዊያን በሁለቱም ፆታ የብር ሜዳሊያውን ለመውሰድ ጣልቃ የገቡ ቢሆንም የወርቅና የነሃስ ሜዳሊያው የኢትዮጵያዊያኑ ሆኗል፡፡

በወንዶች ምድብ ኢትዮጵያዊያኑ  ፍቃዱ ከበበ  በ2፡09፡37 በሆነ ጊዜ የወርቅ ሜዳሊያውን ሲወስድ ሌላው ኢትዮጵያዊ  ሳሙኤል ጌታቸው የነሀስ ሜዳሊያው አግኝቷል፡፡

በተመሳሳይ በሴቶች ምድብ ወርቅነሽ አለሙ በ2፡33፡41 በሆነ ሰዓት አሸናፊ ስትሆን ፣ሌላዋ የአገሯ ልጅ በቀሉ ቤጂ ደግሞ በሶስተኝነት አጠናቃለች፡፡

ትላንት በተካሄደው የሞሮኮው ራባትአለም አቀፍ  ማራቶን ላይ 9ሺህ አትሌቶች መሳተፋቸውን ሽንዋ ዘግቧል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች