ሌስተር በሻምፒዮንስ ሊጉ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለ

መጋቢት 06፣2009

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የመልስ ጨዋታውን ከሲቪያ ጋር ያደረገው ሌስተር በድምር ውጤት 3ለ2 በመርታት ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀሏል፡፡

ጁቬንቱስም ፖርቶን 3ለ0 ረቶ ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀለ ቡድን ሆኗል፡፡ ሌስተር ትናንት በሜዳው ያደረፈገውን ጨዋታ 2ለ0 ነው ያሸነፈው፡፡

ከሳምንት በፊት ከሜዳው ውጭ 2ለ1 መሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡ በምሽቱ ጨዋታ ሌስተር በሞርጋን እና አርበርተን ግቦችን አግኝቷል፡፡

ለሲቪያ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ የወጣው ናስሪ ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን ሲያደርግ አምሽቷል፡፡ ሲቪያ በተለይ በጨዋታው ማጠናቀቂያ ያገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት ኑዛዚ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

በመሆኑም ሌስተር፣ ሪያል ማድሪድ፣ ባርሲሎና፣ ባየር ሙኒክ፣ ዶርቱመንድ እና ጁቬንቱስ ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀሉ ቡድኖች ሆነዋል፡፡

ዛሬ ሁለት ቡኖች ይጠበቃሉ፡ የሻምፒዮንስ ሊጉ የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ የሚቀጥሉ ሲሆን ሞናኮ ከማንችስትር ሲቲ /3ለ5/ ፣አትሌቲኮ ማድሪድ ከባየር ሊቨርኩሰን/4ለ2/ ይጫወታሉ፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች