ማንችስትር ሲቲ ከሻምፒዮንስ ሊጉ ተሰናበተ

መጋቢት 07፣2009

በምሽቱ የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ወደ ፈረንሳይ ተጉዞ ሞናኮን የገጠመው ማንችስተር ሲቲ ከሜዳ ውጭ ብዙ ባገባ በሚለው ህግ ከውድድሩ ወጥቷል፡፡

በጨዋታው ሲቲ 3ለ1 ሽንፈት ያስተናገደ ሲሆን ድምር ውጤቱ 6ለ6 ሆኗል፡፡

ሞናኮ ሁለቱን ግቦች በመጀመሪያው ግማሽ በምባቢ እና ታቫረስ ሲያገኝ፣ በሁለተኛው ግማሽ ባካያኮ ያስቆጠራት የጭንቅላት ኳስ ሲቲን ከውድድሩ አስወጥታለች፡፡

ለሲቲ ሳኔ ጨዋታውን ያልቀየረች ኳስ ከመረብ አገናኝቷል፡፡

ማንችስተር ሲቲ የጨዋታ ብልጫ ቢኖረውም ለግብ የቀረበ ሙከራ በማድርግ የተሻለ አልንበረም፡፡ አጉየሮ የሲቲን አጋጣሚ ሲያመክን ታይቷል፡፡

ሞናኮ ከእንግሊዝ ክለቦች ጋር በተገናኘባቸው የሻምፒዮስ ሊጉ ጥሎ ማለፍ  ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ክብረ ወሰኑን አስቀጥሎ ወጥቷል፡፡

የቢቢሲ እግር ኳስ ተንታኝ ፊል ኔቪል ሲቲ የተጠበቀውን ያህል እየኖረ አይደልም ብሏል፡፡

በሁለተኛው ግማሽ የፈጠርናቸውን ዕድሎች መጠቀም አልቻልንም፣ ቡድናችን ልምድ ያንሰዋል፣ የጋርዲዮላ አስተያይት ነው፡፡

ባየር ሊቨርኩስን እና አትሌቲኮ ማድሪድ ባደረጉት የምሽቱ ሌላኛው  ጨዋታ ያለግብ ተጠናቋል፡፡ በመሆኑም አትሌቲኮ ማድሪድ በመጀመሪያው ጨዋታ ባስመዘገበው የ4ለ2 ውጤት ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል፡፡

ሶስት ቡድኖች  ከስፔን፣ ሁለት ከጀርመን እንዲሁም ከጣሊያን፣ ከእንግሊዝ እና ከፈረንሳይ አንድ አንድ ቡድኖች ቀጣዩን ዙር ተቀላቅለዋል፡፡

ዛሬም የኢሮፓ ሊግ ጨዋታዎች ቀጥለው ይካሄዳሉ፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች