ማዳጋስካራዊው አህመድ አህመድ የካፍ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

የማዳጋስካር እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት የነበሩት አህመድ አህመድ 7ኛው የካፍ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ፡፡

ምርጫው የተካሄደው ዛሬ በአዲስ አበባ ነው፡፡

አህመድ ደምፅ መስጠት ከሚችሉት 54 ሀገሮች የ34ቱን ድምፅ ማግኘት ችለዋል፡፡

የአህመድ ምርጫ የካሜሮናዊውን ኢሳ አሃያቱን የ29 ዓመታት የፕሬዝዳንትነት ዘመን የሚቋጨው ሆኗል፡፡

ካፍ አዲስ ፕሬዝዳንት ማግኘቱ ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ተጠብቋል፡፡

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን /ካፍ/ 60ኛ ዓመት የምስርታ በዓሉንም በአዲስ አበባ እያከበረ ይገኛል፡፡


 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች