የገንዘቤ ዲባባ የአንድ ማይል ክብረ ወሰን ማረጋገጫ ተሰጠው

መጋቢት 8፣ 2009

ገንዘቤ ዲባባ ባለፈው ዓመት ስዊድን ስቶክሆም ላይ ያስመዘገበችው የአንድ ማይል ክብረ ወሰን  በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌደሬሽን ማረጋገጫ ተሰጠው፡፡

የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ማህበር ባወጣው መረጃ መሰረት ነው ገንዘቤ በቤት ውስጥ ሩጫ አንድ ማይሉን 4 ደቂቃ ከ 13 ሰከንድ ከ 31 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው አዲስ የአለም ክብረ ወሰን የሰበረችው፡፡

ገንዘቤ ከ27 ዓመታት በፊት ሮማናዊቷ ዶኢና ሜሊኒቲ ይዛው የነበረችውን ክብረ ወሰን ነው በ4 ሰነኮንዶች ያሻሻለችው፡፡

በሌላ የቤት ውስጥ ውድድር ከገንዘቤ ጋር ተመሳሳይ ቀንና ቦታ በ1000 ሜትር አዲስ ክብረ ወሰን ያስመዘገበው የጅቡቲው አያንለህ ሱሌማንም ክብረ ወሰኑ ተረጋግጦለታል፡፡

በሴቶች 20 ኪ.ሜ ጎዳና ውድድር እና ግማሽ ማራቶን ኬንያዊቷ ፔሪዝ ጄብቼርትር ያስመዘገቡት ክብረወሰን ከተገጋገጠላቸው መካከል ናቸው፡፡ 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች