ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ምድብ ድልድል አለፈ

መጋቢት 10፣ 2009

በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ 10 ስአት ላይ ከኮንጎው ኤሲ ሊዮፓርድስ ጋር ያደረገው ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ምድብ ድልድል ማለፉን አረጋገጠ።

በ2017ቱ የቶታል አፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ የሲሸልሱን ኮቲዲኦር በደርሶ መልስ በመርታት ወደ ጥሎ ማለፉ የገባው ቅዱስ ጊዮርጊስ፥ ኤሲ ሊዮፓርድስን ባሳለፍነው ሳምንት በዶሊሴ ከተማ 1 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል።

ፈረሰኞቹ ዛሬ ደግሞ በሳልሃዲን ሰኢድ ጎሎች 2 ለ 0 በማሸነፍ አጠቃላይ ውጤታቸውን 3 ለ 0 በማድረግ ነው ወደ ምድብ ድልድሉ ያለፉት፡፡

ሳልሃዲን ጎሎቹን ከእረፍት በፊት በ16ኛው ደቂቃ  እና በጨዋታው መጠናቀቂያ አካባቢ በ93ኛው ደቂቃ ነበር ያስቆጠረው፡፡

በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል በዶሊሴ ከተማ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ ያስቆጠረው ምንተስኖት አዳነ በቀይ ካርድ በመውጣቱ ምክንያት በዛሬው ጨዋታ አልተሰለፈም።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ሻምፒዮንስ ሊጉ ምድብ ድልድል በማለፉ 550 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ያገኛል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሮበርት ኦዶንካራ፣ ፍሬዘር ካሳ፣አስቻለው ታመነ፣ ሳልሃዲን በርጊቾ፣ አበባው ቡታቆ፣ አብዱልከሪም ኒኪማ፣ ናትናኤል ዘለቀ፣ አዳነ ግርማ፣  በሀይሉ አሰፋ፣ ሳልሃዲን ሰኢድ እና ፕሪንስ ሲቬሪንሆን በቋሚ አሰላለፍ ይዞ ነው ወደ ሜዳ ገባው፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች