ቬንገር በኤፍኤ ካፕ አዲስ ክብረ ወሰን ያዙ

ግንቦት 20፤2009

አርሰን ቬንገር 7ኛውን የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ በማንሳት የራሱን ክብር ወሰን አሻሽለዋል፡፡

ትላንት ምሽት በዌንብሌይ ስታዲየም በተካሄደ የኤፍ ኤ ካፕ የፍጻሜ  ጨዋታ  አርሰናል ቼልሲን 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ 13 የኤፍኤ ዋንጫውን ማንሳት ችሏል፡፡

በጨዋታው አልክሲስ ሳንቼዝ አርሰናልን ቀዳሚ ያደረገች አከራካሪ ጎል ገና ጨዋታው በተጀመረ በ4ኛው ደቂቃ አስቆጥሮ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል፡፡

በሁለተኛ አጋማሽ ቼልሲዎች ቪክተር ሞስስ በሁለት ቢጫ ካርድ  ከሜዳ በመውጣቱ ቀሪው የጨዋታ ጊዜ በ10 ተጫዋች ማጠናቀቅ  ግድ ሆኖባቸው ነበር፡፡

በ76 ደቂቃ ዲያጎ ኮስታ ቼልሲዎች የ2010 የኤፍ ኤ ዋንጫ እና የፕሪምየር ሊጉ ዋንጫ ያነሱበት የውድድር ዓመት ለመድገም ተስፋ የሰጠች ጎል ማቆጠር ችሏል፡፡

ጨዋታ ሊጠናቀቅ በቀሩት ጥቂት ደቂቃ ራምሴ ከዥሩድ የበተሻገረለት ኳስ የማሸነፊያዋን ጎል ማስቆጠር ችሏል፡፡

በውድድር ዓመቱ ብዙ ትችት ያስተናገዱት ቬንገር የአርሴናል ቆይታቸው በሚቀጥለው ሳምንት በሚካሄደው የክለቡ ቦርድ ስብሰባ የሚወሰን እንደሆነ ለቢቢሲ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች