ሴራሊዮን ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ መሪ ሆነች

ሰኔ 04፣2009

ለ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከኢትዮጵያጋር በምድብ ሰ የተመደበችው ሴራሊዮን ኬኒያን 2ለ1 በማሸነፍ ለጊዜው የምድቡ መሪ ሆናለች፡፡

በዚሁ ምድብ ጋና ከኢትዮጵያ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ዛሬ በኩማሲ የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

ሌሎች ዋና ዋና ውጤቶችን ስንመለከት ሴኔጋል ኢኳቶሪያ ጊኒን 3ለ0፤ ማሊ ጋቦንን 2ለ1፤ ካሜሮን ሞሮኮን 1ለ0፤ ሊቢያ ሲሸልስን 5ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል፡፡

በለሎች በምድብ ጨዋታዎች ያልተጠበቁ ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን ጠንካራዎች ብሄራዊ ቡድኖች በሜዳቸው ተሸንፈዋል፡፡

እነሱም ናይጄሪያ በደቡብ አፍሪካ 2ለ0፤ ኮትዲቯር በጊኒ 3ለ2 እንዲሁም ዛምቢያ በሞዛምቢክ 1ለ0 በሜዳቸው ተሸንፈዋል፡፡

ቱኒዚያ ከግብጽ፤ አልጄሪያ ከቶጎ እና ጋና ከኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጨዋታዎች ደግሞ ተጠባቂ ናቸው፡፡

ምንጭ ቢቢሲ፤ ካፍ
Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች