ከባዱን ሽንፈት በኩማሲ የቀመሱት ዋልያዎቹ ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ

ሰኔ 05፣2009

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ወደ ጋና ኩማሲ አቅንቶ በጋና አቻው 5ለ0 ተረቷል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በወሩ የዓለም እግር ኳስ ደረጃቸው ጋና 49ኛ፣ ኢትዮጵያ ደግሞ 125ኛ ሆነው ተቀምጠዋል፡፡

ዋልያዎቹ በምሽቱ ጨዋታ ቅንጅት አልባ ሆነው ታይተዋል፡፡ አሰልጣኙ በመጨረሻ አካባቢ ያደረጉት ቅያር ቡድኑን በተወሰነ ደረጃ አነቃቅቶታል፡፡

የጋናው አምበል አሳሙሃ ጊያን ለሀገሩ 50ኛ ግቡን በምሽቱ ጨዋታ አስቆጥሯል፡፡

በጨዋታው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተከላካይ ክፍል እና ግብ ጠባቂው  ተደጋጋሚ ስህተት ሲሰራ አምሽቷል፡፡

የመሃል ክፍሉ እና አጠቂው ቅንጅትም በጋናውያን ተጨዋቾች የተሰበረ ሆኖ ታይቷል፡፡

5 ግቦችን ያስተናገደው የዋልያዎቹ ግብ ጠባቂ አቤል ማሞ በጉዳት ተቀይሮ ወጥቷል፡፡

ውጤቱ ኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታት ካስመዘገበችው  የእግር ኳስ ውጤት የከፋው ሆኗል፡፡

ጭቃማው የኩማሲ ሜዳ ዋልያዎቹን አስቸጋሪ ውድድር እንዲያደርጉ ያስገደዳቸው ይመስላል፡፡

ቡድኑ ነገ አዲስ አበባ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡

በዚሁ ምድብ የምትገኘው ሴራሊዮን ኬኒያን 2ለ1 መርታቷ ይታወሳል፡፡

በአዝመራው ሞሴ

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች