ቻይና በአትሌቲክሱ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት ማቀዷን ገለጸች

ሰኔ9፤2009

ቻይናና ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ዘርፍ ተባብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን ግንኙነት እየፈጠሩ መሆኑን በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ለዥንዋ ገለፁ፡፡

አምባሳደር ላ ዪፋን የሁለቱን ሀገራት ስፖርት ዘርፍ ለማስተሳሰር ከኢትዮጵያ መንግስት መሪዎች ጋር እየተነጋገሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በግንኙነቱ ኢትዮጵያ በተለይ በረዥም ርቀቶች ያላትን ልምድ ለቻይና ማካፍል እንደምትችል ተገልጿል፡፡

በተለይ በማራቶን የሚወዳደሩ ቻይናውያን በኢትዮጵያ መጥተው ልምምድ መስራት ይፈልጋሉ ብለዋል አምባሳደሩ ፡፡

ከቻይና ደግሞ በሌሎች ውድድሮች ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን ማግኘት ይቻላል ተብሏል፡፡

ምንጭ፡-ዥንዋ

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች