ጅማ ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፕሪሚየር ሊጉን ተቀላቀሉ

ሐምሌ 3፣2009

ጅማ ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ  ፕሪሚየር ሊጉን መቀላቀላቸውን አረጋገጡ።

ጅማ ከተማ ወልቂጤ ከተማን  3ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ  የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ መሆኑን አረጋግጧል።። ለጅማ ከተማ  ሄኖክ መሀሪ በ36 እና 48 ደቂቃ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር አቅሌስያስ ግርማ ሶስተኛውን የጅማ ከተማ ጎል አስቆጥሯል። ጅማ አባ ቡና ከፕሪምየር ሊጉ ያጣችው ጅማ ከተማ በፕሪምየር ሊጉ ተወካይ ማግኝት ችላለች፡፡

የወልቅጤ ከተማ ብቸኛ ጎል አክሊሉ ተፈራ በ89ኛው ደቂቃ አስቆጥሮ ጨዋታው በጅማ ከተማ አሸናፊነት ተጥናቋል። ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከመቀሌ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ 1 ለ1 ተለያይተዋል፡፡

ለመቐለ ከተማ በ67ኛው ደቂቃ አስራት ሽገሬ  ሲያስቆጥር አለም አንተካሳ ለወልዋሎ በ93 ደቂቃ የአቻነቱን ጎል አስቆጥሯል።

በዚህም ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በቀጥታ ፕሪሚር ሊጉን መቀላቀል ችሏል። ሀዲያ ከተማ ከሀላባ 0ለ0 በመለያየታቸው ከመቐለ ከተማ ጋር በሚቀጥለው ማክሰኞ ወደ ፕሪምየር ሊጉ የሚቀላቀል  ሶስተኛ ክለብ ለመሆን ድሬዳዋ ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡  የከፍተኛ ሊጉ ጨዋታውችም ማክሰኞ የሚጠናቀቁ  ይሆናሉ፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች