የሀላባ ከነማ አቤቱታ ዛሬ ውሳኔ ያገኛል

ሐምሌ 5፣2009

በከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ የመጨረሻ ጨዋታውን ከሀድያ ሆሳህና ጋር ያደረገው ሀላባ ከነማ  ያቀረበው አቤቱታ ዛሬ መልስ እንደሚያገኝ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታወቀ፡፡

የክሱ ምክንያት የሀድያ ሆሳዕናው ሄኖክ አርፋጮ ከሶስት ጨዋታ በፊት የተጋጣሚን ቡድን በመማታቱ የአራት ጨዋታ እና የ4ሺህ ብር ቅጣት ተላልፎበት ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ሀድያ ሆሳዕና ክለብ ባቀረበው  ይቅርታ አድርጉልኝ ጥያቄ መሰረት ፌደሬሽኑ ለተጫዋቹ ይቅርታ ማድረጉን ለሀድያ ሆሳዕና ደብዳቤ ፅፋል፡፡

ነገር ግን ይህ ተጨዋች ባለፈው ሰኞ ሀድያ ሆሳዕና ከሀላባ በተጨወቱበት ወቅት በመሰለፉ ሀላባ ከነማ  ክስ አቅርቧል፡፡

የሀላባ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ማስረጃም  በዲስፒሊን መመሪያው መሰረት ከመሰለፉ በፊት ተጨዋቹ ቢያንስ  የቅጣቱን ግማሽ ማድረግ ይኖርበት እንደነበር ያስረዳል፡፡

በመሆኑም የፌደሬሽኑ የድስፕሊን ኮሚቴ ጉዳዩን እየመረመረ መሆኑን እና ዛሬ ውሳኔ እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

ሁለቱ ክለቦች ባለፈው ሰኞ ጨዋታቸውን 0ለ0 በመፈጸማቸው ሀድያ ሆሳዕና ክለብ ሶስተኛ ሆኖ ፕሪሚየር ሊጉን ለመቀላቀል የድሬዳዋውን ጨዋታ ይጠብቃል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች