ፈደሬሽኑ ሀላባ ከነማን ክስ ውድቅ አደረገ

ሐምሌ 5፣2009

በከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ የመጨረሻ ጨዋታውን ከሀድያ ሆሳህና ጋር ያደረገው ሀላባ ከነማ  ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ ማድረጉን ዛሬ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታወቀ፡፡

የክሱ ምክንያት የሀድያ ሆሳዕናው ሄኖክ አርፋጮ ከሶስት ጨዋታ በፊት የተጋጣሚን ቡድን ተጫዋች በመማታቱ የአራት ጨዋታ እና የ4ሺህ ብር ቅጣት ተላልፎበት ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ሀድያ ሆሳዕና ክለብ ተጫዋች ባቀረበው  የይቅርታ አድርጉልኝ ጥያቄ መሰረት ምህረት እንደተደረገለት ነው ፌደሬሽኑ ያስታወቀው፡፡

ሌላው ውድቅ የተደረገው ክስ ደግሞ የሃዲያ ሆሳዕናው ተጫዋች አስራት ሚሻሞ በተለያዩ ጨዋታዎች ላይ አምስት የቢጫ ማስጠንቀቂያ ካርድ ተሰጥቶት ከሃላባ ከነማ ጋር በተደረገው ጨዋታ ላይ ተሰልፏል የሚል ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ተጫዋቹ የተመለከተው የቢጫ ማስጠንቀቂያ ካርድ አምስት አልሞላም በማለት የከፍተኛ ሊግ ኮሚቴው ምላሽ ሰጥቷል፡፡

የሀላባ ከነማ እግር ኳስ ክለብ በዲስፒሊን መመሪያው መሰረት ተጨዋቹ በጨዋታው ላይ ከመሰለፉ በፊት ተጨዋቹ ቢያንስ  የቅጣቱን ግማሽ ተቀጥቶ መጨረስ ይኖርበታል የሚል መከራከሪያ አሁንም እያነሳ ይገኛል፡፡

በዚህ ምክንያትም ፈደሬሽኑ የዲስፕሊን መመሪውን በመጣስ ይህንን ውሳኔ አሳልፏል ነው ያለው፡፡

በአዝመራው ሙሴ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች