በአለም አትሌቲክስ ታዳጊዎች ሻምፒዮና የኢትዮጵያ እና ኬኒያ ትንቅንቅ ታይቶበታል

ሐምሌ 10፣2009

በኬኒያ ናይሮቢ በተካሄደው 10ኛው የዓለም ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ እና ኬኒያ ታዳጊዎች ትንቅንቅ የሁለቱን ሀገራት የወደፊት ፍጥጫ ያመላከተ ሆኗል፡፡

ሁለቱም ሀገራት በተመሳሳይ 4 ወርቅ ውድድራቸውን ጨርስዋል፡፡

ኢትዮጵያም 4 የወርቅ፣ 3 የብርና 5 የነሃስ ሜዳሊያ በድምሩ 12 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች፡፡ ኬኒያ በ4 ወርቅ፣ 7 ብር እና 4 ነሕስ መሰብሰብ  ችላለች፡፡

በመሆኑም ኢትዮጵያ አዘጋጇን ሃገር ኬንያን ተከትላ 5ኛ በመሆን ውድድሩን በድል አጠናቃለች፡፡

ደቡብ አፍሪካ 5 ወርቅ፣ 3 ብር እና 3 ነሐስ በማግኘት የሻምፒዮናው ፈርጥ ሆናለች፡፡ ቻይና እና ኩባ በተመሳሳይ የወርቅ ብዛት ይከተላሉ፡፡

10ኛው የዓለም ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና 131 የዓለም አገራት ተሳትፍዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 25ቱ በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ስማቸውን አስፍረዋል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች  ለልዑካን ቡድኑ አቀባበል አድርገውለታል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች