ወደ ፕሪሚየር ሊግ የሚቀላቀለው ቀሪ አንድ ቡድን ነገ ይለያል

ሐምሌ 10፣ 2009

                   ፎቶ፡‑ የሀዲያ ሆሳዕናና ሀላባ የስፖርት ክለቦች 

ነገ በድሬዳዋ ከተማ በሚካሄደው የከፍተኛ ሊግ ማጠቃለያ ውድድር ቀሪው የኢትዮጰያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ቡድን ይለያል፡፡

ከቀኑ 8 ሰዓት የሚጫወቱት መቀሌ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና ሊጉን የመቀላቀል ዕድል ያላቸው ቡድኖች ናቸው፡፡

መቀሌ ከተማ አዲሱን ስታዲዮም በፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ለማድመቅ ጠንካራ ፍልሚያ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡

ባለፈው ዓመት ከፕሪሚየር ሊግ የወረደው ሀድያ ሆሳዕና በአንፃሩ ከችግሮቹ መውጣቱን የሚያሳይበት ጨዋታ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

ሊጉን እንደተቀላቀሉ ያረጋገጡት የምድብ ሀ አሸናፊ ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ እና የምድብ ለ አሸናፊው ጅማ ከተማ ደግሞ ለክብር ከቀኑ 10 ሰዓት ይጫወታሉ፡፡

ድሬዳዋ ከተማ ከብሔራዊ ሊግ ወደ ከፍተኛ ሊግ የሚያድጉ ቡድኖችን ለመለየት የሚደረግ ጨዋታንም እያስተናገደች ነው፡፡ 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች