መቀሌ ከተማ ፕሪሚየር ሊጉን ተቀላቀለ

ሃምሌ 11፤2009

የ2009 ዓ.ም የከፍተኛ ሊግ ማጠናቀቂያ ጨዋታ 3ኛውን  የፕሪሚየር ሊጉን ተሳታፊ ክለብ የመቀሌ ከተማ መሆኑን አረጋግጧል ፡፡

በምድብ ሀ 2ኛ ሆኖ ያጠናቀቀው የመቀሌ ከተማ የምድብ ለ 2ኛ የሆነውን ሀዲያ ሆሳዕናን  2ለ1 በመርታት ለዚህ ድል በቅቷል ፡፡

ውጤቱን ተከትሎ በምድብ ሀ የሚገኙት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እና መቀሌ ከተማ ቡድኖች የፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ቡድኖች መሆናቸውን አሳውቋል፡፡

መቀሌ ከተማ የፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ሲሆን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ፡፡

ተሸናፊው ሀድያ ሆሳህና በአንድ አመት ውስጥ የፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ለመሆን  ያደረገው ጥረት አልተሳካትም ፡፡

የመቀሌ ከተማ ቡድን በመጪው አመት ለሚያደርጋቸው የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች በከተማው ያስገነባውን አዲስ ስታዲየም በመጠቀም የሊጉን ጨዋታ የሚያደምቅ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በመሆኑም ጅማ ከተማ ፣ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እና መቀሌ ከተማ ፕሪሚየር ሊጉን የተቀለቀሉ ቡድኖች መሆናቸው ተረጋግጧል ፡፡

በአዝመራው ሙሴ 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች