የካፍ ፕሬዝዳንት ከጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ጋር መከሩ

ነሐሴ 1፣ 2009

የአፍሪካ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አህመድ አህመድ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳላኝ ጋር በአፍሪካ እግር ኳስ እና በኢትዮጵያ ሚና ዙሪያ መከሩ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ትናንት  ምሽት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያ ለእግር ኳሱ ዕደገት እየተሰሩ ስላሉ ተግባራት በጠቅላይ ሚኒስትሩ  ለፕሬዝዳንቱ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

ሀገሪቱን  ለአህጉራዊ ውድድሮች ዝግጅቹ  የሚያደርጋትን የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እያከናወነች መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፅዋል፡፡

የካፍ ፕሬዝዳንት አህመድ አህምድ ከጠቅላይ ሚኒስትር  ኃይለማሪያም ደሳላኝ ጋር ከመምከራቸው በፊት የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ፣ የአደይ አበባ ስታዲየም ግንባታን እና የካፍ ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

የካፍ ፕሬዝዳንት ጉብኝት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ዕድገት ሚና እንደሚኖረው ተጠብቋል፡፡

በጉብኝቱ የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ ርዕስቱ ይርዳው፣ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌድሬሽን ፕሬዝደንት ጁኒይዲ በሻ እና የካፍ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል መሳተፋቸው የፌደሬሽኑ ህዝብ ግንኙነት አቶ ወንድምኩን አላዩ ለኢቢሲ ገልጸዋል፡፡

በአዝመራው ሞሴ

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች