ዛሬ ምሽት በአውሮፓ ሱፐር ካፕ ሪያል ማድሪድ ከማንችስተር ዩናይትድ ይጫወታሉ

ነሃሴ 02፤ 2009

የዩሮፓ ሊግ አሸናፊ የሆነው ማንችስተር ዩናይትድ ከአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ሪያል ማድሪፍ ጋር  ለአውሮፓ ሱፐር በሜቄዶኒያ ስኮፒያ ከተማ ዛሬ ምሽት 3፡45 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ማንችስተር ዩናይትድ የሱፐር ካፕ ዋንጫ ለሁለተኛ ጊዜ ለማንሳት ሪያል ማድሪድን ያስተናግዳል፡፡

በቅደመ ዝግጅት ውድድር በባርሴሎና ከተሸነፈ ወዲህ ሌሎች ጨዋታችን ማሸነፈ የቻለው ዩናይትድ በአንጻሩ ሪያል ማድሪድ  በወዳኝነት ጨዋታው ድል ሊቀናው አልቻለም፡፡

ሪያል ማድሪድ ለክርስቲያኖ ሮናልዶ የሰጠው እረፍት ባይጠናቀቅም በምሽቱ ጨዋታ ላይ እንደሚሰለፍ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ተናግሯል፡፡

በዩናትድ በኩል ኤሪክ ባይ እና ፊል ጆን በቅጣት የማይሰለፉ ሲሆን አዲሱ ፈራሚያቸው ኒማኒያ ማቲች ይሰለፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የዩናይቱዱ አማካኝ ኤነሪክ ሚኪታሪያን የሱፐር ካፕ ዋንጫ ድላችን በፕሪምየር ሊጉ የሚኖረን አስፈሪነት ቀድመን የምናሳውቅበት ይሆናል የሚል አስተያየቱ ሰጥቷል፡፡

በአውሮፓ የሱፐር ካፕ ሪያል ማድሪድ 3 ጊዜ ዋንጫውን ማንሳት ሲችል ማንችስተር ዩናይትድ አንድ ጊዜ አሸናፊ መሆን ችለዋል፡፡

ጆዜ ሞሪንሆ ሶስት ክለቦች ይዘው ለሱፐር ካፕ ፍጻሜ በማድረስ ብቸኛው አሰልጣኝ መሆን ቢችሉም ባለድል መሆን አልቻሉም፡፡

የዘንድሮውን የሱፐር ካፕ አሸናፊ ከሆኑ ግን አዲስ ታሪክ ያጽፋሉ ማለት ነው፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች