የኢትዮጵያ አትሌቶች በምሽቱ ማጣሪያ ይሳተፋሉ

ነሐሴ 03፤2009

5ኛ ቀኑን በያዘው 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለት የማጣሪያ ውድድሮች ዛሬ ምሽት ትሳተፋለች፡፡

ውድድሮቹ የወንዶች 5 ሺህ ሜትር እና የሶስት ሺህ መሰናክል ሴቶች ማጣሪያ  ናቸው፡፡

ምሽት 1 ሰዓት ከ5 የሴቶች 3 ሺህ መሰናክል ማጣሪያ ይካሄዳል፡፡

በውድድሩ ሶፊያ አሰፋ፣ እቴነሽ ዲሮ እና ብርቱካን ፈንቴ ኢትዮጵያን ወክለው ይሰለፋሉ፡፡

ምሽት 4 ሰዓት ከ05 ደግሞ የወንዶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ ይካሄዳል።

ሙክታር እድሪስ፣ ሰለሞን ባረጋ፣ ዮሚፍ ቀጀልቻ እና ሀጎስ ገብረህይወት በሚካሄደው ማጣሪያ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡ በዚህ ውድድር በ10ሺህ ሜትር ወርቅ የወሰደው ሞፋራህ ይሳተፋል፡፡

ኢትዮጵያ በ10ሺህ ሴቶች ወርቅ እና ብር እንዲሁም በወንዶች ማራቶን ብር በማግኘት በሜዳሊያ ሰንጠረዡ 5ኛ ናት፡፡

አሜሪካ እና ኬኒያ በ3 ወርቅ ሰንጠረዡን እየመሩ ነው፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች