ሻምፕዮኑ ቼልሲ ሲሸነፍ አዲስ የተቀላቀለው ኸድርስፊልድ ድል ቀንቶታል

ነሃሴ 6፤2009

ዛሬ በተደረጉት የመጀመሪያ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የአምናው ሻምፕዮን ቼለሲ በሜዳው በበርንሌይ የ3ለ2 ሽንፈት ደርሶበታል፡፡

ቼልሲ በሜዳው ይሸነፋል ተብሎ ያልተገመተ ሲሆን ጋሪ ካሄልና ሴስክ ፋብሪካስ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግደውበታል፡፡

በአንጻሩ አዲሱ የሊጉ አባል ኸደርስፊልድ ክሪስታል ፓላስን 3ለ0 በማሸነፍ የሊጉን የመጀመሪያ ድል አጣጥሟል፡፡

በሌሎች ጨዋታዎችም ኤቨርተን ስቶክን 1ለ0፤ ዌስትብሮም በርን ማውዝን 1ለ0 ማሸነፍ የቻሉ ክለቦች ናቸው፡፡

ሳውዝ ሃምፕተን ከስዋንሲ ዜሮ ለዜሮ እንዲሁም ዋትፎርድ ከሊቨርፑል 3ለ3 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

ብራይተን ከማንቸስተር ሲቲ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

እሁድ ደግሞ ኒውካስትል ዩናይትድ ከቶተንሃም እንዲሁም ማንቸስተር ዩናይትድ ከዌስትሃም ይጫወታሉ፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች