ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ወርቅ በሙክታር ኢድሪስ አገኘች

ነሃሴ 6፤2009

በአምስት ሺህ በተደረገው የፍጻሜ ውድድር ሙክታር ኢድሪስ ሞፋራህን በማስከተል ለኢትዮጵያ ሁለተኛውን ወርቅ ማስገኘት ችሏል፡፡ 13:32.79 ሙክታር የገባበት ሰዓት ነው፡፡

በውድድሩ የቡድን ስራ በመስራት አስተዋጽኦ ያደረጉት ዩሚፍ ቀጀልቻና ሰለሞን በርጋ አራተኛ እና አምስተኛ መውጣት ችለዋል፡፡

በውድድሩ ዮሚፍ 13:33.51 ሰዓት ያስመዘገበ ሲሆን ሰለሞን 13:35.34 ማስመዝገብ ችሏል፡፡

16ኛውን የለንደን አትሌቲክስ ሻምፒዮናን በማሸነፍ ከአትሌቲክሱ አለም ለመሰናበት ያቀደው ሞፋራህ ህልሙ በሙክታር ተጨናግፎበታል፡፡

ሞፋራህ 13:33.22 ሰዓት በማስመዝገብ የብር ሜዳሊያ ማግኘት ችሏል፡፡

ውድድሩን ሶስተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው አሜሪካዊው ፓውል ኪፕኮሜ ነው፡፡ 13:33.30 የገባበት ሰዓት ነው፡፡

በ5 ሺህ ሜትር በሙክታር የተገኘው ወርቅ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ፣ ኬንያና ፖላንድ በመቀጠል በአለም አራተኛ ደረጃ እንድትቀመጥ አድርጓታል፡፡

ኢትዮጵያ እሰካሁን 2 የወርቅና 2 የብር በአጠቃላይ 4 ሜዳሊያዎችን ማግኘት ችላለች፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች