አርሰን ቪንግር በሊቨርፑል የደረሰባቸውን ሽንፈት ተከትሎ የደጋፊዎቻቸውን እምነት ጠየቁ

ነሐሴ 22፣2009

በሶስተኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሊቨርፑል የ4ለ0 ሽንፈት የቀመሱት የአርሰናሉ አለቃ አርሰን ቪንግር የደጋፊዎችን እምነት ጠይቀዋል፡፡

ቪንግር ደጋፊዎች በቡድኑ እምነት እንዳያጡ ነው የጠየቁት፡፡

የእግር ኳስ ተንታኙ ሮቢ ሳቤጅ ለቢቢሲ በሰጠው ቃለ መጠይቅ ሊቨርፑል አርስናልን አሸነፈው ሳይሆን አጠፋው ነው የሚባለው ሲል ገልጿል፡፡

በሶስት ጨዋታዎች ሲስት ነጥብ ብቻ ያገኘው አርስናል በሊጉ 16ኛ ደረጃ ተቀምጧል፡፡ አሌክስ ሳንቸዝ ዳግም በአርስናል መለያ መጫወቱ የመልቀቁን ነገር አጠራጣሪ አድርጎታል፡፡

ጣፋጭ ድል ከአርሰናል የወሰደው ሊቨርፑል በበኩሉ በ7 ነጥብ ወደ ሊጉ አናት ላይ እንዲመጣ አድርጎታል፡፡

በሁሉም ጨዋታዎች ድል እየቀናው የመጣው ማንችስተር ዩናይትድ በ9 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው፡፡

ዌስት ሃም በሶስቱም ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዶ በሊጉ ግርጌ ላይ ነው፡፡

የሊጉ ጨዋታዎች ለቀጣይ ሁለት ሳምንታት በሀገራት የተለያዩ ማጣሪያ ውድድሮች ይቋርጣል፡፡

 

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች