የዶርቱመንዱ ኦስማን ደንበሌን ጓዙን ጠቅልሎ ወደ ባርሴሎና አቀና

ነሐሴ 22፣2009

ባርሲሎና የቦርሲያ ዶርቱመንዱን የፊት መስመር ተጨዋች ኦስማን ደምበሌን 135.5 ሚሊዮን ዩሮ ሊደርስ በሚችል የዝውውር ዋጋ የግሉ አደረገ፡፡

ባርሲሎና ለ20 ዓመቱ ወጣት መነሻ የዝውውር ክፍያ 96.3 ሚሊዮን ዩሮ ከፍሏል፡፡

የደምበሌ የዝውውር ዋጋ ከኔማር 200 ሚሊዮን ዩሮ በመቀጠል ሁለተኛው ውዱ ተጨዋች አስብሎታል፡፡

ባርሲሎና ወደ ፓርሴን ጀርመን ያቀናውን ብራዚላዊ ኔማር ለመተካት ደንበሌን ማስፈረማቸው ተነግሯል፡፡

ደንብሌ ፊርማውን ካስቀመጠ በኋላ በባርሲሎና መጫወት ደስተኛ እንደሚያደርገው መናገሩን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች