በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጅማሮ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች ድል ተቀዳጅተዋል

መስከረም 03፣2010

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጅማሮ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች ድል ተቀዳጅተዋል፡፡

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጅማሮ ማንችስተር ዩናይትድ በሜዳው የስዊዝዘራልዱን  ባዜል አስተናግዶ 3ለ0 አሸንፏል፡፡

በምድብ አንድ የሚገኘው የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች ማርዋን ፌይላኒ፣  ሮሜሉ ሉካኩ እና ማርከስ ራሽፎርድ ጎሎቹን አስቆጥረዋል። ወጣቱ ማርከስ ራሽፎርድ ለዩናይትድ በቻምፒዮንስ ሊግ በፕሪምየር ሊግ በኤፍ ኤ ካፕ በዩሮፓ ሊግ እና በሊግ ካፕ በማስቆጠር አዲስ ክብረ ወሰን ማስመዝገብ ችሏል፡፡

በምድብ ሁለት የሚገኘው ፒ ኤስ ጂ በሴልቲክ ፓርክ  ከስኮትላዱ ሴልቲክ  ጋር ባደረገው ጨዋታ  5 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡

ለፒ ኤስ ጂ ኔይማር  ፣ ኪሊን ምባፔ ፣ ኤዲንሰን ካቫኒ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር ፣ የሴልቲክ ሚካኤል ለስቲግ  በራሱ መረብ ላይ  5ተኛው ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው በፒ ኤስ ጂ የበላይነት ተጠናቋል፡፡

በሌላ የምድቡ ጨዋታ  ባየር ሙኒክ በአሊያንዝ አሬና የቤልጄሙ አንደርሌክትን 3ለ0 ሲረታ ሎዋንዶውስኪ፣ ቲያጎ አልካንትራ እና ጆሽዋ ኪሚችበ የጎሎቹ ባለቤቶች ሆነዋል።

በምድብ 3 የሚገኘው የአንቶኒ ኮንቴው ቼልሲ የአዘርባጃኑ ካራባህ 6 ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡

ፔድሮ ሮድሪጌዝ፣ ዳቪድ ዛፓኮስታ፣ ሴዛር አዝፕሊኩዌታ፣ ባካያኮ እና ሚቺ ባሽዋዬ የቼልሲን ጎሎች ሲያስቆጥሩ ሜድቬዴቭ በራሱ ጎል ላይ የቼልሲን የመጨረሻ ጎል አስቆጥሯል፡፡በዚው ምድቡ የሚገኙት  ሮማ እና አትሌቲኮ ማድሪድ ጨዋታቸውን 0ለ0 በሆነ ውጤት አጠናቀዋል፡፡

በምድብ አራት የሚጠበቀው  የባርሴሎና እና የጁቬንቱስ ጨዋታ በባርሴሎና አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ከ78 ሺህ በላይ ተመልካች በተከታተለው  ይህ ጨዋታ  ሊዮኔል ሜሲ የጨዋታው ኮከብ መሆን ችሏል፡፡

በጨዋታው አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ 2 ኳሶችን ከመረብ ሲያሳርፍ ፥ ክሮሺያዊው ራክቲች ቀሪዋን ጎል አስቆጥሯል፡፡

በዚህ ምድብ የሚገኘው ስፖርቲንግ ሊዝበን  ወደ ግሪክ ተጉዞ  ኦሎምፒያኮስን   3ለ2 ማሸነፍ ችሏል ረቶ ተመልሷል።

በቻምፒየን ሊጉ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽትም ቀጥለው ሲደረጉ በምድብ 5 ሊቨርፑል በሜዳው  የስፔኑ ሴቪያን ያስተናግዳል፡፡በዚሁ ምድብ  የስሎቬኒያው ማሪቦር ስፓርታክ ሞስኮን ያስተናግዳል፡፡

በምድብ 6  ማንችስተር ሲቲ   ከሜዳው ውጭ ከፌይኖርድን ሲያስተናግድ የፖርቱጋሉ ፖርቶ ከቱርኩ ቤሺክታሽ ፣ የጀርመኑ አር ቢ ላይብዚሽ ከሞናኮ በምድብ 7 የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፡

በምድብ 8 የአምናው አሸናፊ  ሪያል ማድሪድ የቆጵሮሱ አፖይል ኒኮሲያን በቤርናባው ሲያተናግድ የእንግሊዙ ቶትንሀም ሆትስፐር ከጀርመኑ ቦርሲያ ዶርትመንድ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታም ዛሬ ምሽት ከሚጠበቁ ጨዋታዎች ውስጥ ነው።

ሁሉም ጨዋታዎች ምሽት 3 ሰዓት ከ45 ይጀምራሉ።

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች