ጥሩነሽ ዲባባ የቺካጎ ማራቶንን በአስደናቂ ብቃት አሸነፈች

መስከረም 28፣2010

ጥሩነሽ የቺካጎ ማሮቶንን በተከታታይ ለሶስተኛ ጊዜ ለማሸነፍ ትሮጥ የነረችውን ፍሎረንስ ኪፕላጋትን በረጅም ርቀት ጥላ በመግባት ማሸቨፍ ችላለች፡፡

ያለ አሯሯጭ 42 ኪሎ ሜትሩን ብቻዋን እየመራች መጨረስ የቻለችው ጥሩነሽ 2:18:31 የገባችበት ሰዓት ነው፡፡

ኬንያዊቷ ብሪጊድ ኮስጌ በ2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ22 ሰከንድ ሁለተኛ ስትሆን፥ አሜሪካዊቷ ጆርዳን ሃሳይ በ35 ሰከንዶች ዘግይታ ሶስተኛ በመሆን ውድድሯን ጨርሳለች።

በወንዶቹ ምድብ ደግሞ አሜሪካዊው ጋለን ሩፕ በ2 ሰዓት ከ09 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ በመግባት አሸናፊ ሆኗል።

ኬንያውያኑ ኪሩይ እና በርናርድ ኪፕየጎ ደግሞ ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን አጠናቀዋል።

ጥሩነሽ 2:17:56 ሰዓት በማስመዝገብ በአለም ሶስተኛው ፈጣን ሰዓት ባለቤት መሆኗ ይታወሳል፡፡

ውድድሩ ብርቱ ፍኩክር ያልነበረበት መሆኑና አሯሯጮች ያለመኖራቸው የጠበቀችውን ሰዓት ማስመዝግብ አለመቻሏን ጥሩነሽ ተናግራለች፡፡

በቀጣይ የርቀቱን ክብረ ወሰን ለመስበር እንምትሰራ በስፍራው ለነበሩት ጋዜጠኞች ገልጻለች፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች