አርጀንቲና የዓለም ዋንጫ ተሳታፊነቷን አረጋገጠች

ጥቅምት 01፣2010

አርጀንቲና በአውሮፓውያኑ 2018 በሩሲያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ተሳታፊነቷን አረጋግጣለች።

በ2018  ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ውድድሮች ትናንት ምሽት በደቡብ አሜሪካ ሀገራት መካከል ቀጥለው ተካሂደዋል።

አርጀንቲና በሊዮኔል ሜሲ ሶስት ጎሎች ነው የዓለም ዋንጫ ተሳታፊነተን ያረጋገጠችው።

በሜዳዋ አርጀንቲናን ያስተናገደችው ኢኳዶር 3ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች።

ጨዋታው በተጀመረ በ38ኛው ሰከንድ በኢባራ አማካንኝት ባስቆጠሩት ጎል ኢኳዶር 1ለ0 መምራት ችለው የነበሩ ሲሆን ሊዮኔል ሜሲ በ12ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ጎል የአርጀንቲናውያንን ተስፋ አለምለማለች። ሜሲ  በጨዋታው በ20ኛው እና በ62ኛው ደቂቃ ባስቆጠራቸው ጎሎች አርጀንቲና  ዓለም ዋንጫን መቀላቀል ችላለች።

ሌላው በደቡብ አሜሪካ ሀገራት መካከል በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ጨዋታ ብራዚል ቺሊን 3ለ0 አሸንፋታላች። ውጤቱን ተከትሎ የሁለት ጊዜ የኮፓ አሜሪካ ሻምፒዮኗ ቺሊ ከ2018 የዓለም ዋንጫ ውጭ ሆናለች።

በሌሎች ጨዋታዎች ኡራጉዋይ 4- 2 ቦሊቪያን ፣ ፔሩ1 -1 ኮሎምቢያ፣ፓራጉዋይ1-0 ቬንዙዌላ በሆነ ውጤት ጨዋታቸው አጠናቀዋል።

ከደቡብ አሜሪካ ሀገራት ብራዚል፣ አርጀንቲና፣ ኡራጉዋይ  እና ኮሎምቢያ ዓለም ዋንጫውን መቀላቀላቸው አረጋግጠዋል።

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች