ኦሮሚያና መከላከያ የጃን ሜደ አለም አቀፍ አገር አቋራጭ 10 ኪ.ሜ ውድድርን አሸነፉ

የካቲት 05፣  2009

ኦሮሚያ ክልልና መከላከያ ስፖርት ክለብ   የጃን ሜደ አለም አቀፍ አገር አቋራጭ 10 ኪ.ሜ ውድድርን በበላይነት አጠናቀቁ።

1ሺህ ዘጠኝ ተወዳዳሪዎች የተካፈሉበት 34ኛው የጃን ሜደ አለም አቀፍ አገር  አቋራጭ ውድድር ዛሬ ረፋድ በአራት የተለያዩ ምድቦች ተከፍሎ  ተካሂዷል።ከውድድሮቹ  ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ  የድብልቅ ዱላ ቅብብል  በውድድሩ ተካቷል።

ቀደም ብሎ  ብሎ  በተካሄደው  የሴቶች  6 ኪሎ  ሜትር  ሩጫ ውድድር የትራንስ ኢትዮጵያዋ ለተሰንበት ግደይ ቀደሚ በመሆን ስታጠናቅቅ፣ዘይነባ  ይመር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና  ሀዊ ፈይሳ  ከመከላከያ ሁለተኛና  ሶስተኛ  ሆነው አጠናቀዋል።

በ8 ኪ.ሜ ወጣት ወንዶች ምድብ  ደግሞ   ከኦሮሚያ ተፈራ ሞሲሳ አሸናፊ ሆኗል። ሰለሞን ቢረጋ ከደቡብ ሁለተኛ ሆኖ  ሲያጠናቅቅ፣ ሰለሞን በሪሁን  ከትራስ  ኢትዮጵያ ተከታዮን ደረጃ ወስዷል።

በ10 ኪሎ ሜትር  አዋቂ   ወንዶች መከላከያን የወከለው  ጌታነህ ሞላ ቀዳሚ ሆኖ መግባት ሲችል፣አበራ ሀዲስ ከትራንስ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል።የሞሰቦ  ሲሚንቶው ሞገስ ጥዑማይ ደግሞ  ሶስተኛ ደረጃን አግኝቷል።

በሴቶች የምድቡ ውድድር ደግሞ  ኦሮሚያ ክልልን የወከለችው ደራ ዲዳ በበላይነት ስታጠናቅቅ ፣ በላይነሽ ኦልጂራ  ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተከታዩ  ደረጃ አግኝታለች።የአማራ ክልል ተወካዩዋ   በገበያነሽ አየለ የሶስተኛ ደረጃነትን አግኝታለች።

አሸናፊዎቹ   ከሰባት ወራት በኃላ  በዩጋንዳ ካምፓላ በሚካሄደው  አለም አገር አቋራጭ ውድድር  ኢትዮጵያን የሚወክሉ ይሆናል።

ሪፖርተር ፥ ንዋይ ይመር

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች