ከ18 ዓመት በታች የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፉ አትሌቶች ወደ ኬንያ አቀኑ

ሐምሌ 03፣2009

የፊታችን እሮብ ኬንያ በሚካሄደው የአለም ከ18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ዛሬ  ወደ ኬንያ አቀኑ፡፡

ኢትዮጵያ በ12 ወንድ በ11 ሴት በድምሩ በ23 አትሌቶች ነው በዉድደሩ የምተወከለው፡፡

በ10ኛው የዓለም ታዳጊ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በየሁለት ዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን ዘንድሮ ለ10ኛ ጊዜ ከሀምሌ 5 ጀምሮ በኬንያ  ሞ አለም አቀፍ የስፖርት ማዕከል ይካሄዳል፡፡   

በሻምፒዮናዉ ከአለም አገራት የተወጣጡ ዕድሜያቸዉ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ከ1600 በላይ አትሌቶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከሀምሌ 5 ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው የአለም የታዳጊ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የፊታችን እሮብ የሚጀመር ሲሆን ኢትዮጵያ የምትሳትፍበት  የ3000 ሜትር ሴቶች የፍፃሜ ዉድድር በመክፈቻው ይካሄዳል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች