በፊፋ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሩሲያ ኔው ዜላንድን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈች

ሰኔ 11፤2009

ትላትን በተጀመረው የፊፋ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ አዘጋጇ ሩሲያ ኔውዜላንድ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸነፈች፡፡

ለአስረኛ ጊዜ እየተካሄደ ባለው የፊፋ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ስምንት ሀገሮች በሁለት ምድብ ተከፍፍለው ጨዋታቸው ያደርጋሉ፡፡

የፊፋው ፕሬዝዳንት ዝያኒ ኢፋቲኖ ባደረጉት ንግግር አዘጋጇ ሩሲያ በሴንት ፒተርስበርግ ስታዲየም ኒውዜላንድን አስተናግዳ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች፡፡

ጨዋታው በተጀመረ በ30 ደቂቃ የኒውዜላንዱ ሚካኤል ቦክሳል በራሱ ጎል ላይ ባስቆጠራት ጎል ሩሲያ ቀዳሚ ሲያደርጋት በ69 ደቂቃ ሞሉቭ ሁለተኛውን ጎል በማስቆጠር ሩሲያን ሙሉ ሶስት ነጥብ ይዛ እንድትወጣ አድርገዋታል።

ጨዋታው የሩሲያ ፕሬዝዳንት እንዲሁም ብራዚላዊው የኳስ ጥበበኛ ፔሌ ተከታትለውታል፡፡

በዚህ ምድብ የአውሮፓ ቻምፒዮን ፖርቹጋል ከኮንካፍ ቻምፒዮን ሚክሲኮ ጋር ዛሬ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ የሪያል ማድሪዱ ክርስያኖ ሮናልዶ በጨዋታው እንደሚሰለፍ ይጠበቃል፡፡

በምድብ ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ካሜሮን ከኮፓ አሜሪካ ቻምፒዮን ከሆነችው ቺሊ ጋር ዛሬ ጨታቸውን ያደርጋሉ፡፡ ነገ የአለም ዋንጫ አሸናፊዋ ጀርመን ከአውስትራሊያ ጋር ትገጥማለች፡፡

የፊፋ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እ.ኤ.አ በ2005 የተጀመረ ሲሆን ቀጣዩ የዓለም ዋንጫ አስተናጋጅ በሆነችው ሀገር ይስተናገዳል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች