Back

የኢትዩዽያ ቡና ስፖርት ክለብ ስራ አስፈፃሚ እና ምክትላቸው በገዛ ፍቃዳቸው ከሀላፊነታቸው ለቀቁ

ጥር 30፡ 2011 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ስራ አሰፈፃሚ የሆኑት መቶ አለቃ ፍቃዱ ማሞ እና ምክትላቸው አቶ ይስማሸዋ ስዩም በገዛ ፍቃዳቸው ከሀላፊነቻቸው ለመነሳት መልቀቂያ አስገቡ፡፡

ኢትዮጵያ ቡና በፕሪምየር ሊግ በተደጋጋሚ ሽንፈት በማስተናገዱ እና ከደጋፊዎ በደረሰባቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ምክንያት ለእዚህ ወሳኔ እንዳደረሳቸው ገልፀዋል፡፡

የደጋፊዎች ቦርድ ጥር 28 ባካሄደው ስብሰባ ላይ መቶ አለቃ ፍቃዱ ማሞ በይፋ ክለቡን ለመልቀቅ መገደዳቸውን አስታውቋል፡፡