አትሌት አልማዝ አያና የ2017 ምርጥ አትሌቶች እጩ ሆነች

መስከረም 23፣2010

አትሌት አልማዝ አያና የ2017 ምርጥ አትሌቶች እጩ ሆነች።

በየአመቱ የአለም ምርጥ አትሌቶችን እየመረጠ የሚሸልመው አለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የ2017 አስር የወንድ እና 10 ሴት አትሌቶችን ይፋ አድርጓል፡፡

በለንደን በተካሄደው 16ኛው አለም አቀፍ ቻምፒዮና 10ሺ ሜትር ያሸነፈችው  ኢትዮጵያዊቷ  አልማዝ አያና የዓመቱ ምርጥ የሴት አትሌት ዕጩ  በመባል በአንደኝነት ተመርጣለች፡፡

ሄለን ኦብሪ ከኬንያ፣ ሳሊይ ፒርሰን ከአውስትራሊያ ሳንድራ ፔርኮቪች፣ ካስተር ሴሜንያ ከደቡብ አፍሪካ፣  ከክሮሽያ ብሪትኒ ሪሴ እንዲሁም ከአሜሪካ ኢካትሪን ስቲፋንዲ ከግሪክ ዝርዝር ውስጥ የገቡ የሴት አትሌቶች ናቸው፡፡

በወንዶች እጩዎች ዋይድ ቫን ኒከርክ ከደቡብ አፍሪካ፣ ሙታዝ ባርሺም ከኳታር፣ ፓዌል ፋጄክ ከፖላድ፣ ሞፋራ ከብሪታንያ፣ ሳም ኬንድሪክስ ከኬንያ፣ ሉቮ ማንዮነጋ ከደቡብ አፍሪካ እንዲሁም ኦመር ከጃማይካ ክሪስታን ታይለር በዝርዝሩ ተካተዋል፡፡

በለንደን በተካሄደው 16ኛው አለም አቀፍ ቻምፒዮና ላይ በ100 ሜትር አሸናፊ የሆነው አሜሪካዊ ጀስቲን ጋትሊን በዝርዝሩ ውስጥ አልተካተተም፡፡

በዕጩነት ከቀረቡ 20 አትሌቶች መካከል የተሻለ ደምጽ የሚያገኙት የፊታችን ታህሳስ ወር በፈረንሳይ ሞናኮ ከተማ በወንድና በሴት ምርጥ የሚለውን ስያሜ ያገኛሉ።

ባለፈው አመት በሴቶች አልማዝ አያና በወንዶች ደግሞ ጃማይካዊው ዩዜን ቦልት የዓመቱ ምርጥ አትሌቶች በመባል መመረጣቸው ይታወሳል።

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች