በ2020 ኦሊምፒክ የድብልቅ ጾታ ውድድሮች እንዲካተቱ ተወሰነ

ሰኔ 2፤2009

ጃፓን በምታዘጋጀው የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ላይ ወንዶች ሴቶች በአንድ ስፖርታዊ ውድድር አይነት ላይ ተደባልቀው እንዲወዳደሩ መወሰኑን አለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

ይህ ውሳኔ ተግባራዊ እንዲደረግ ከተወሰነባቸው የስፖርት ውድድር አይነቶች መካከል አትሌቲክስ፤ ውሃ ዋና፤ የጠረጴዛ ቴኒስና ትሪያትሎን ይገኙበታል፡፡

ከአትሌቲክስ ውስጥ አራት በአራት በ400 ሜት የዱላ ቅብብሎሽና አራት በ100 ሜትር የውሃ ዋና በድብልቅ ጾታ እንዲካነው ተመስኗል፡፡

የአለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ቶማስ ባች እንደገለጹት ከሆነ ይህ ውሳኔ መተላለፉ ውድድሩን የበለጠ ጠቃሚና ሴቶችን በብዛት ተሳታፊ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ቶኪዮ ከሪዮ ኦሊምፒክ በበለጠ አምስት አዳዲስ የስፖርት ውድድሮችን በማካተት 33 የስፖርት ውድድሮችን የምታስተናግድ ስትሆን በአጠቃላይ 15 የውድድር አይነቶች ተከታዋል፡፡

የአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌደሬሽን በበኩሉ በዱላ ቅብብል ውድድሮች የድብልቅ ጾታዎች ፍክክር እንዲካተት መወሰኑን ቢደግፈውም በተግባራዊነቱ ላይ ግን አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ገልጿል፡፡

በመሆኑም በኦሊምፒክ ቁጥር አንድ የሆነው የአትሌቲክስ ውድድር እንዳይደበዝዝ ከአለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር እንደሚሰሩ የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት ሰባስቲያን ኮይ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች