ሞሮኮ የ2026ቱን የአለም ዋንጫ ለማዘጋጀት እንደምትፈልግ ገለፀች

 ነሐሴ 05፣2009

ሞሮኮ የ2026ቱን የአለም ዋንጫ ለማዘጋጀት በይፋ ጥያቄ እንደምታቀርብ ገለፀች፡፡

የሞሮኮ እግር ኳስ ፌደሬሽን ዛሬ ይፋ እንዳደረገው  ከ8 ዓመት በኃላ የሚካሄደውን የአለም እግር ኳስ ዋንጫ ለማዘጋጀት ጥያቄ እንደምታቀርብ ይፋ አድርጓል፡፡የአለም አቀፉ እግር ማህበር ፊፋም ሞሮኮ ውድድሩን ለማዘጋጀት ፍላጎት ካላት እንደሌሎች አገራት ለመወዳደር እንደምትችል ይሁንታውን መስጠቱ ተመልክቷል፡፡

የአፍረካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ኳፍም ለለሞሮኮ ከወዲሁ ድጋፉን እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

ሞሮኮ ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ የ2010ሩን የአለም ዋንጫ ጨምሮ ለአራት ጊዜ ያህል የአለም ዋንጫን ማዘጋጀት ጥያቄ አቅርባ ተቀባይነት ሳታገኝ ቆይታለች፡፡

እ.ኤ.አ በ2026 የሚካሄደውን የአለም ዋንጫ ለማዘጋጀት እንደሚፈልጉ አሜሪካ፣ ካናዳና ሜክሲኮ  ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡

ሞሮኮ ጥያቄዋ ተቀባይነት የሚያኝ ከሆነ ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል የአለም እግር ኳስ ዋንጫን ያዘጋጀት ሁለተኛው አገር ትሆናለች፡፡

በውድድሩ አሁን ላይ የሚሰተፉት አገራት ቁጥር ከነበረበት 32 ፣ወደ 48 የሚያድግበት በመሆኑ በዓይነቱ የመጀመሪያ ያደርገዋልም ተብሏል፡፡

ምንጭ፡ ሲጂቲኤን

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች