Back

ጋና የ2025ቱን የአፍሪካ ዋንጫ እንደምታዘጋጅ የካፍ አስታወቀ

ታህሳስ 30፣ 2011 ዓ.ም

የ2023ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ታዘጋጃለች ተብላ ስትጠበቅ የነበረችው ጋና የ2025ቱን አፍሪካ ዋንጫ እንደምታዘጋጅ የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ አህመድ አስታወቁ፡፡

የጋናው ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ የ2023ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ለማዘግየት መስማማታቸውንም ለካፍ በላኩት ደብዳቤ ገልፀዋል፡፡  

በዚህ መሰረት አቶ አህመድ ለጋዜጠኞች እንደ ተናገሩት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድርን ለማዘጋጀት ከጫፍ ከደረሱ ሀገራት መካከል ካሜሮን 2021 አዘጋጅነትን እድል ማግኝቷን አስታውቀዋል፡፡

ካፍ ይፋ ካደረገው አዳዲስ ለውጦች መካከል አይቮሪ ኮስት የ2023 ካሜሮን ደግሞ የ2021 ውድድር እንዲያዘጋጁ ቅድሚያ መስጠቱን አስታውቋል፡፡

ካፍ እ.ኤ.አ በጥር 9 የዚህን ዓመት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር አዘጋጅነት ለግብፅ እና ለሳውዝ አፍሪካ ቀዳሚነቱን መስጠቱ የሚታወቅ ነው፡፡

ግብፅ የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ሀገር መሆኑዋን ካፍ አስታውቋል፡፡