Back

በዶፒንግ ተጠርጥረው እገዳ ተጥሎባቸው የነበሩ 37 የሩሲያ አትሌቶች በግል እንዲወዳደሩ ተፈቀደላቸው

ሀምሌ 03 2011

በሩሲያ የአበረታች መድሃኒት ተጠቅመዋል በሚል የዓለም አቀፉ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽኖች ማህበር ከሚያዘጋጃቸው ዉድድሮች እንዳይሳተፉ ታግደው የነበሩ 37 የሩሲያ አትሌቶች በግላቸው ፍቃድ ያለው ነፃ አትሌት ሆነው እንዲወዳደሩ ተፈቀደላቸው፡፡

37ቱም የሩሲያ አትሌቶች በየትኞችም ዓለም አቀፍ ዉድድሮች እ..ኤ.አ. በ2019 ሀገራቸዉን ሳይወክሉ እንደ ነፃና ፍቃድ ያለው አትሌት ሆነው መሳተፍ እንዲችሉ የአለም አቀፉ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽኖች ማህበር የአበረታች ማድሃኒትና ቅመሞች ቦርድ ወስኗል፡፡

እስካሁን 117 የሩሲያ አትሌቶች በዚህ እድል ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡

 

ይሁን እንጂ አቤቱታ ከቀረቡ አትሌቶች መካከል የ40ዎቹ ቅሬታ ግን ዉድቅ ተደርጓል፡፡
 

የሩሲያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን በሀገሪቱ  ስፖርተኞች አበረታች መድሃኒት እንዲጠቀሙ አድርጓል በሚል እ.ኤ.አ በ2015 የተጣለበት ማእቀብ  አሁንም የፀና መሆኑን የአለም አቀፉ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽኖች ማህበር አስታውቋል፡፡