ኢትዮጵያን በሪዮ ኦሎምፒክ የሚወክሉ 43 አትሌቶች ተመረጡ

ሐምሌ 8፣ 2008

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ኢትዮጵያን በሪዮ ኦሎምፒክ የሚወክሉ 43 አትሌቶችን መርጧል፡፡

ኢትዮጵያ በማራቶን፣ በ10ሺህ እና 5ሺህ ሜትር፣ 3ሺህ መሰናክል፣ 8 መቶ ሜትር እንዲሁም 1ሺህ 5 መቶ ሜትር በሁለቱም ጾታ የሚካፈሉ አትሌቶቿን አሳውቃለች፡፡

በ20 ኪሎ ሜትር እርምጃ ደግሞ ኢትዮጵያ በሁለት ሴት አትሌቶች ተካፋይ ትሆናለች፡፡ አልማዝ አያና እና ጥሩነሽ ዲባባ በአንድነት በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች ኢትዮጵያን ለመወከል በምርጫው ተካተዋል፡፡

ጥሩነሽ ዲባባ በ5ሺህ ሜትር ተጠባባቂ ስትሆን አልማዝ አያና በሁለቱም ርቀቶች የምትወዳደር ይሆናል፡፡

በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ይገረም ደመላሽ፣ ታምራት ቶላ፣ አባዲ ሃዲስ ሲመረጡ ኢብራሄም ጀይላን ተጠባባቂ በመሆን ተመርጧል፡፡

በተመሳሳይ በወንዶች 5ሺህም ሙክታር እድሪስ፣ ደጀን ገ/መስቀል፣ ሃጎስ ገ/ህይወት፣ ሲካተቱ ባዲ ሃዲስ ተጠባባቂ ሆኗል፡፡

ገንዘቤ ዲባባ በ1ሺህ 5 መቶ ሜትር ኢትዮጵያን እንድትወክል ተመርጣለች፡፡ በ8 መቶ ሜትር ወንዶች ደግሞ መሃመድ አማን ተካቷል፡፡

የሪዮ ኦሎምፒክ ከ20 ቀናት በኋላ በብራዚል ይጀመራል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች