ጣሊያን ከ59 ዓመታት በኋላ ከዓለም ዋንጫ ውጪ ሆነች

ህዳር 05፤2010

የአራት ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ጣሊያን ከ59 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዓለም ዋንጫ ውድድር ውጭ ሆነች፡፡

ጣሊያን ከሜዳዋ ውጭ በስዊዲን የደረሰባትን የ1ለ0 ሽንፈት ትናንት በሜዳዋ ለመቀልበስ ያደረገችው ጥረት ጨዋታው 0ለ0 በመጠናቀቁ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

ጣሊያኖች ውጤቱን ለመቀልበስ ያደረጉት ተደጋጋሚ ጫና ውጤት አልባ ሆኖ አምሽቷል፡፡ በመሆኑም በደርሶ መልስ ድምር ውጤት ጣሊያን 1ለ0 ተሽንፋ ከውድድሩ ወጥታለች፡፡

ውጤቱ ጣሊያናያዊያንን በእንባ ሲያራጭ፣ ሲዊዲኖቹን አስፈንድቋል፡፡

አንጋፋው የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ቡፎን ከጨዋታው በኋላ ከብሔራዊ ቡድን መለያየት እንዳሰበ የብዙሃን መገናኛዎች እየዘገቡ ነው ፡፡

ከስዊዲን ብሔራዊ ቡድን መለያየቱ ሲነገር የከረመው ዘላታን ኢብራሄሞቪች በተቃራኒው ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ወደ ሩሲያ ሊያቀና እንደሚችል ተዘግቧል፡፡

የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን አራት ጊዜ የዓለም ዋንጫን ማንሳት የቻለ ሲሆን፣ ከዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ውጭ ሲሆን ደግሞ እ.አ.አ ከ1958 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች