የቀድሞው የፊፋ አመራር አባል የነበሩት ቻክ ብሌዘር በ72 ዓመታቸው አረፉ

ሐምሌ 6፤2009

በቀድሞው የፊፋ አመራር ውስጥ አባል የነበሩት አሜሪካዊው ቻክ ብሌዘር በ72 ዓመታቸው መሞታቸው ተገለጸ፡፡

 እ.ኤ.አ. በ2015 ብሌዘር ከማንኛውኛውም የእግር ኳስ እንቅስቃሴ የታገዱ ሲሆን በካንሰር በሽታ ሲሰቃዩ ቆይተው በ72 አመታቸው ማረፋቸው ተነግሯል፡፡

እ.ኤ.አ በ2013 በጉቦ፤ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና በግብር ማጭበርበር ጥፋተኛ የተባሉት ብሌዘር የፊፋ የሙስና ቅሌቶችን ለማጋለጥ መሰማማት ችለው ነበር፡፡

ብሌዘር የሰሜን እና መካመለኛው አሜሪካ የእግር ኳስ ማህበር ሃላፊ የነበሩ  ሲሆን እሳቸው በሰጡት መረጃ 14 ሴፍ ብላተርን ጨምሮ የቀድሞ የፊፋ አመራር አባላት ከስልጣናቸው እንዲነሱ ተደርጓል፡፡

በ2013 የሰሜን እና መካመለኛው አሜሪካ የእግር ኳስ ማህበር ኮንካፋ ባወጣው መረጃ ቻክ ብሌዘር ከ1996- 2011 ድረስ ለቤት ኪራይና ለተለያዩ ክፍያዎች ከ16 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ መቀበሉ ታውቋል፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች