16 ሀገራትን የሚያሳትፈው ቱር መለስ የብስክሌት ውድድር በሀዋሳ ተጀመረ

ነሐሴ 23፣2009

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ5ኛ ጊዜ የሚደረገው ቱር መለስ ለአረንጓዴ ልማት የብስክሌት ውድድር የ16 ሀገራትን ብስክሌተኞች በማሳተፍ በሀዋሳ መደረግ ጀመረ፡፡

ውድድሩ በጠቅላላው 574 ኪ.ሜትር እንደሚሸፍን ታውቋል፡፡

መነሻ እና መድረሻውን ሀዋሳ ከተማ ያደረገው በመጀመሪያው ቀን የ120 ኪ.ሜትር ውድድር ኢትዮጵያዊው ሬድዋን ሳለህ 1ኛ በመሆን አሸንፏል፡፡ የኬኒያ እና የደቡብ አፍሪካ ብስክሌተኞች ተከታለው ገብተዋል፡፡

ውድድሩ ከነሐሴ 22 እስከ 27፣2009 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን የደቡብ እና የኦሮሚያ አካባቢዎችን የሚያዳርስ ነው፡፡

ብስክሌተኞቹ ከውድድራቸው በኋላ የችግኝ ተከላ ማካሄዳቸው ታውቋል፡፡

ምንጭ፡‑ የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር

 

 

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች