34ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና የፊታችን እሁድ ይካሄዳል

የካቲት 02፣2009

34ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና የፊታችን እሁድ የካቲት 5/2009 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

ፌዴሬሽኑ  በሰጠው መግለጫ ውድድሩ አለም አቀፍ ደረጃዉን በጠበቀ ሁኔታ ለማካሄድ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል።

ዉድድሩ የሀገር ዉስጥ አትሌቶችን ብቃት ለመፈተሽና ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶችን ለመለየት አጋዥ መሆኑን የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኃይሌ ገብረስላሴ ተናግሯል፡፡

በዘንድሮው ሀገር አቀፍ ሻምፒዮና የሚሳተፉ አትሌቶች ቁጥር ከዓምናው የተሻለ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን ለአሸናፊ አትሌቶችም በአጠቃላይ የ320 ሺ ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል ተብሏል፡፡

አምስት የዉድድር ዘርፎችን ባካተተው በዘንድሮው ሻምፒዮና በድምሩ 1ሺህ 209 አትሌቶች ይሳታፋሉ ተብሏል፡፡

ከ1ኛ እስከ 4ኛ ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ አትሌቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተመርጠው በጥሩነሽ አካዳሚ ስልጠና ወስደው ኡጋንዳ ለምታዘጋጀው አገር አቋራጭ ዉድድር ኢትዮጵያን የሚወክሉ ይሆናል፡፡

ዉድድሩን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን  በቀጥታ ስርጭቱ ያስተላልፋል፡፡

ሪፖርተር:- ላሉ ኢታላ

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች