ዮሚፍ፣ ሰሎሞንና ሙክታር ኢድሪስ ወደ ፍጻሜ ውድድር አለፉ

ነሐሴ 03፣2009

ዛሬ በተካሄደው የወንዶች 5 ሺህ ሜትር የማጣሪያ  ውድድር ሙክታር እድሪስ፣ ሰለሞን ባረጋና ዮሚፍ  ቀጀልቻ  ወደ ፍጻሜ ውድድር አልፈዋል፡፡

በምድብ አንድ አምስት ሺህ ሜትር ማጣሪያ ውድድር የተሳተፉት ኢትዮጵያውያኑ ከምድባቸው አንደኛ እና ሶስተኛ በመሆን ነው ወደ ፍጻሜው ውድድር ያለፉት፡፡

ውድድሩን ዮሚፍ ቀጀልታ አንደኛ  ሙክታር እድሪስ  3ተኛ በመሆን አጠናቀዋል፡
የ10 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሞፋራህ ውድድሩን ሁለተኛ በመሆን አጠናቋል፡፡

በሁለተኛው ምድብ የተወዳደረው ሰለሞን ባረጋም ከምድቡ 1ኛ በመውጣት ወደ ቀጣይ ዙር አልፏል።

በሻምፒዮናው ኢትዮጵያ በአንድ የወርቅና ሁለት የብር ሜዳልያዎች ከአለም አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ከአፍሪካ ደግሞ ከኬንያና ደቡብ አፍሪካ ቀጥላ 3ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች