6 ሜዳሊያዎችን የሰበሰበው የኢትዮጵያ ሉዕክ አዲስ አበባ ገባ

የካቲት 14፣ 2009

ከየካቲት 5 እስከ 12 በግብፅ ሲካሄድ በሰነበተው የአፍሪካ ዓመታዊ የብስክሌት ሻምፒዮና  ስድስት ሜዳሊያዎችን ያገኘው የኢትዮጵያ ሉዕካን ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

ቡድኑ አዲስ አበባ ሲገባ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡

ኢትዮጵያ በሁለት ወርቅ፣ ሶስት ብር እና አንድ ነሐስ ውድድሯን አራተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡

ሁለት ወርቅ የተገኘው በሴቶች የታዳጊ ውድድር ዘርፍ ነው፡፡

ደቡብ አፍሪካ፣ ኤርትራ እና አዘጋጇ ግብፅ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ኢትዮጵያ በተለይም በወጣቶች ዘርፍ ያሳየችው የበላይነት በውድድሩ አይን እንድትይዝ ማስቻሉ ተገልጿል፡፡

በውድድሩ 20 ሀገራት ተካፍለዋል፡፡

Average (0 Votes)

ተያያዥ ዜናዎች ተያያዥ ዜናዎች