ኢንፍሉዌንዛ ጡንቻዎቻችንን ያዳክማል

4 Yrs Ago
ኢንፍሉዌንዛ ጡንቻዎቻችንን ያዳክማል

በኢንፍሉዌንዛ ወይም በጉንፋን  የሚመጣ  ሳል የጡንቻዎቻችንን  ጥንካሬ ያዳክማል ተባለ፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ በየዓመቱ ከ5 እስከ 10 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች በኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ ይጠቃሉ፡፡ ከነዚህ ሰዎች መካከል በአማካይ 2 መቶ ሺህ የሚደርሱት ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሲሆን 50 ሺህ ያህሉ ደግሞ ለሞት ይዳረጋሉ፡፡

በተለይ እድሜያቸው 65 እና ከዛ በላይ የሆነ ሰዎች ለኢንፍሉዌንዛ ተጋላጭ ናቸው፤ ምክንያቱም እድሜ እየገፋ ሲሄድ በሽታ የመከላከል አቅም እየተዳከመ ስለሚመጣ ነው፡፡

ትኩሳት፣ ሳል፣ የጉሮሮ ህመም፣ ራስ ምታት፣ ከፍተኛ ድካምና ውጋት የኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ ምልክቶች ናቸው ፡፡

የኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ በመተንፈሻ አካላት ላይ ጉዳት ያደርሳል፡፡ በሽታው በአብዛኛው የሚተላለፈው በተለምዶ አፍንጫችንን በእጃችን በመዳበስ ልምዳችን በመታገዝ በንክኪ አማካይነት ነው፡፡

ቫይረሱ በመተንፈሻ አካላት በኩል አድርጎ ወደ ሴሎቻችን ይዘልቃል፡፡ ከዚያም ፕሮቲን የሚያመርቱትን የሴሎቻችንን ክፍሎች በመቆጣጠር መራባትና አጎራባች ሴሎችን መውረር ይጀምራል፡፡

በዚህ ሁኔታ የኢንፍሉዌንዛ ቫይረሱ በሽታ የመከላክል አቅምን በማዳከም በሳንባ ላይ ጉዳት ያደርሳል፡፡

ህክምናው ምንድነው?

  1. ፈሳሽ በብዛት መውሰድ (ውሃ፣ አጥሚትና ጁስ)፤ በተጨማሪም የተለያዩ ጸረ-ቫይረሰ መድሃኒቶች በሀኪም ትዕዛዝ ሊወሰዱ ይችላሉ
  2. እረፍት ማድረግ (በቂ እንቅልፍ ማግኘት በሽታ የመከላከል አቅምን ያሳድጋል)
  3. የህመም ማስታገሻዎችን መውሰድ

ምንጭ፡- cnn.com


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top