ሮታሪ ክለብ አዲስ አበባ ኮቪድ-19ን ለመከላከል እና ለማከም የሚረዱ የሕክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

3 Yrs Ago
ሮታሪ ክለብ አዲስ አበባ ኮቪድ-19ን ለመከላከል እና ለማከም የሚረዱ የሕክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ
ሮተሪ ድጋፍ

 

 

የሮታሪ ክለብ አዲስ አበባ ኮቪድ-19ን ለመከላከል እና ለማከም የሚረዱ 2.2 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የሕክምና ቁሳቁሶችን ዛሬ ለጤና ሚኒስቴር አስረክቧል።

ቁሳቁሶቹ 1 ሺህ 550 ለሕክምና ባለሙያዎች የሚሆኑ አልባሳት፣ ሲም ካርድ መቀበል የሚችሉ 16 ታብሌቶች እና 10 የኦክስጂን ስሊንደሮች ናቸው።

ዛሬ ለጤና ሚኒስቴር የተላለፉት የሕክምና መሣሪያዎቹ 1 ሺህ 100 አልጋ ለያዘው እና በሚሌኒየም አደራሽ ለተዘጋጀው የሕክምና ማዕከል የሚውሉ እንደሆነ ተገልጿል።

የሕክምና መሣሪያዎቹን የተረከቡት የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት መጠናከር እንዳለበት እና ሌሎች አካላትም ድጋፍ ማድረጋቸውን እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

ዶ/ር ሊያ ከሮታሪ ክለብ አዲስ አበባ አባላት ጋር በመሆንም በሚሌኒየም አደራሽ የተዘጋጀውን የሕክምና ማዕከል ጎብኝተዋል።

ሮታሪ ክለብ አዲስ አበባ በቀጣይም ከውጭ ተገዝተው ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ላይ የሚገኙ የኦክስጂን መቆጣጠሪያ መሣሪዎችን እና ለፅኑ ሕሙማን ማቆያ የሚሆኑ አጋዥ መተንፈሻዎችን (ቬንትሌተሮችን) ለተለያዩ ሆስፒታሎች በድጋፍ መልክ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

በዓለም ይልፉ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top